በቤተመንግስት በተዘጋጀው ሽልማት…
✔️ በቤተመንግስት በተዘጋጀው ሽልማት ላይ ሰለሞን ባረጋ የ3ሚሊየን ብር ቶዮታ መኪና ሲሸለም ለሜቻ ግርማ 1ሚሊየን 5 መቶ ሺህ ብር ጉዳፍ ፀጋዬ እና ለተሰንበት ግደይ ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን ብር ሲሸለሙ 4ኛ ለወጣ አትሌት 2መቶ ሺህ ብር ከዚያ በላይ እስከ 8ኛ ለወጣ 150ሺህ ብር ሸልሟል።
ሜዳሊያ ላመጣ አሰልጣኝ ለዋና አሰልጣኝ 2መቶ ሺህ ብር ለምክትል 1መቶ 50ሺህ ብር ሸልሟል።
✔️ አትሌቶቹ በቤተመንግ በካፓ ደምቀው ሽልማታቸውን ወስደዋል።
✔️ እኔም የጋበዘኝ ባይኖርም ድርቅ ብዬ ቤተመንግስት ሄጄ አትሌት ገዛኸኝ አበራ ለሚመለከተው አካል ነግሮልኝ ልገባ ችያለሁ።
ስልክ ይዞ መግባት ስለማይቻል ምስል አላስቀመጥኩም።
✔️ ፕሮግራሙን ፌደራል ስፓርት ኮሚሽን እንዳዘጋጀው ለማወቅ ችያለሁ።
#ብራቮ ስፓርት ኮሚሽን!💪
አሁንስ እኔንም እሩጥ እሩጥ አለኝ!